This page contains information about Department of Small and Local Business Development services for Amharic speakers.
የንግድ ስራዎን ያሳድጉ
የንግድ ስራ ለመጀመር አስበዋል?
የንግድ ስራ ለመጀመር እያሰቡ ነው? የንግድ ስራ ሃሳብዎን በተግባር ለመፈፀም መመሪያ ይሆን ዘንድ ቢዝነስ ዕቅድ (ፕላን) ማዘጋጀት ጥሩ ሃሳብ ነው። በተገቢው ሁኔታ የተዘጋጀ ቢዝነስ ዕቅድ (ፕላን) ስራዎን እንዴት እንደሚያከናውኑ በሚገባ የሚያስቀምጥ ሰነድ ሲሆን ለፋይናንስ ተቋማት እና አጋር ሊሆኑ ለሚችሉ ድርጅቶች ለንግድ ስራዎችዎ ስኬት መመሪያ የሚሆን ሰነድ እንዳልዎ ያሳያል።
የቢዝነስ ዕቅድዎን (ፕላንዎን) በሚጽፉ ጊዜ፣ DSLBD ለማገዝ ዝግጁ ነው። በትናንሽ የቢዝነስ ማዕከል አማካኝነት በግለሰብ ስር ያሉ ቢዝነሶች የእኛን የክትትል እና የስልጠና ሴሚናሮችን ያገኛሉ።
ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን በስልክ ቁጥር 202-727- 3900 ይደውሉ።
ለትናንሽ የቢዝነስ ስራዎች የገንዘብ ምንጮች
የእርስዎ የንግድ ስራ አድጎ ማየት አንፈልጋለን።
በማደግ ላይ ያሉ የንግድ ስራዎች ካፒታል ያስፈልጋቸዋል። በDSLBD፣ የእርስዎን የንግድ ስራ ለማገዝ ዝግጁ የሁሉ የበርካታ የአካባቢያዊ እና የክልላዊ ኔትወርክ ድጋፎች ያገኛሉ። ሁሉን ያካተተ የምክር አገልግሎት እና ትምህርታዊ አውደጥናቶችን እናቀርባለን እንዲሁም ከገንዘብ አበዳሪዎች ጋር እናገናኝዎታለን። ይህም ከማይክሮ ብድር እስከ የቴክኖሎጂ ድጋፍን ያጠቃልላል፣ DSLBD ትናንሽ የንግድ ስራዎች መወዳደር ይችሉ ዘንድ የፋይናንስ ድጋፍን ይሰጣል።
Grants and loans from ከDSLBD የሚገኙ ልገሳዎች እና ብድሮች አካባቢያዊ የንግድ ስራ ባለቤቶች መደብሮቻቸውን እንዲያሻሽሉ፣ የመደብር ስራ ሰዓቶቻቸውን በተቻለ መጠን እንዲያራዝሙ ሊረዳቸው ይችላል። የፋይናንስ እገዛችን ኢላማ ያደረገው የተወሰኑ የአውራጃውን ክፍሎች ለመደገፍ አልያም የተወሰኑ ችግሮችን የተጋፈጡ የንግድ ስራዎችን መደገፍ ነው። በአውራጃ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት የንግድ ስራ ካለዎ፣ ከተወሰኑ ፕሮግራሞቻችን ሊጠቀሙ ይችላሉ።
የትንሽ ንግድ ስራ ማሻሻያ ልገሳ የትንሽ ንግድ ስራ ማሻሻያ ልገሳ (“ፕሮግራሙ”) የሚያከናውነው፦ 1) በስራ ላይ ያሉ ትናንሽ የንግድ ስራዎች መስፋፋትን ይደግፋል ፤ 2) የአውራጃውን የታክስ መሰረት ይጨምራል፤ 3) ለአውራጃ ነዋሪዎች አዲስ ስራን ይፈጥራል፤ 4) የተመሰከረላቸው የንግድ ስራ ኢንተርፕራይዞች እድሎችን ይፈጥራል (CBEs)፤ እና 5) የንግድ ስራዎች ዘላቂነት ያለው የDC እቅድ ግቦችን እንዲያከናውኑ ያበረታታል።
- CBE ማይክሮብድሮች የተመሰከረለት የንግድ ስራ ኢንተርፕራይዝ (የንኢ) ከሆኑ፣ የንግድ ስራዎን ለማሳደግ እስከ $25,000 የሚደርስ ማይክሮ ብድር ሊያግዝዎ ይችላል።
- የጤናማ ምግብ ችርቻሮ የትንሽ የምግብ መቸርቸሪያ መደብር ባለቤት ከሆኑ፣ DSLBD ትኩስ ምርት እንዲገዙ ሊያግዝዎ ይፈልጋል።
- የመደብር መግቢያ ማሻሻያ የንግድ ስራዎ መደብር ትንሽ ያረጀ ይመስላል? ለማደስ እያሰቡ ነው ወይስ የመደብርዎን መግቢያ ማሻሻሉን በቅርቡ አከናውነዋል? በተመረጡ የአውራጃው ክፍሎች የተወሰኑ ወጭዎችን ተመላሽ የሚያደርጉ ፕሮግሞች አሉን።
- የመንገድ ዳር የማስታወቂያ ምስሎች ብድር እርዳታ የእርስዎን ሽያጮች እንዲቀንሱ የDDOT ግንባታ ፕሮጀክት እንዲቀንስ ካረገብዎ፣ ይህ የ$1,000,000 ብድር ሽያጮችን ዳግም እንዲያገኙ፣ ኪራይዎን ለመክፈል እና ያለፉ ውዝፍ ታክሶችን እንዲከፍሉ በስተጎን ተቀምጧል።
ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን በስልክ ቁጥር 202-727- 3900 ይደውሉ።
ሰርተፍኬት ያግኙ
ለCBE ምክር ወረቀት መስፈርቶች ክፍል የሚደረጉ ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፡-
ትናንሸ እና አካባቢያዊ የንግድ ስራዎችን ከDC መንግስት የኮንትራት እድሎች ጋር ማገናኘት።
የተመሰከረለት የቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ (CBE) በመሆን፣ በDistrict of Columbia የሚሰጥ የግዥ እድሎችን ምርጫዎች ያገኛሉ።. የCBE ፕሮግራም በDC መንግስት የኮንትራት እድሎች ውስጥ ቢዚነስዎን በተሻለ የውድድር መድረክ እንዲገኝ ያግዛል።
የCBE ምስክር ወረቀት መስፈርቶች።
ለCBE ምስክር ወረቀት ብቁ እንዲሆኑ፣ ከሌሎች መስፈርቶች በተጨማሪ፣ ቢዝነስዎ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባዋል፦
- የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ዋና ቢሮ በDC ውስጥ መሆን ይገባዋል
- የንግድ ስራው ዋና ስራ አስፈፃሚ እና በከፍተኛ የአስተዳደር ስራ ላይ ያሉ ሰራተኞች በዲስትሪክቱ በሚገኘው ዋና ፅ/ቤት የአስተዳደር ሃላፊነታቸውን ማከናወን ይገባቸዋል።
- ቢዝነሱ ከሚከተሉት አንዱን ማሟላቱን ማሳየት ይኖርበታል፡-
1) የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኞች ከ50% በላይ የሆኑት የዲስትሪችቱ ነዋሪ ናቸው፤
2) የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ባለንብረቶች ከ50% በላይ የሆኑት የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች ናቸው፤ ወይም፣
3) ከባንክ ሂሳቦች በስተቀር፣ የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ከ50% በላይ ነብረቶች በዲስትሪክቱ ውስጥ ይገኛሉ፤ እናም የቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ጠቅላላ ገቢዎች ከ50% በላይ የሚሆኑት የዲስትሪክቱ ጠቅላላ ገቢዎች ናቸው።
ለአዲስ አመልካቾች CBE ለመሆን የሚከተሉትን ሂደቶችን ያከናውናሉ፦
1. መወሰድ የሚገባውን የCBE ቅድመ ምስክር ወረቀት መግለጫዎችን (ዳግም ምስክር ለማግኘት፣ ለማሻሻል፣ እና ለጥምር አገልግሎት ምስክር ወረቀት)፤
2. Submit the የቀጥታ መስመር CBE ማመልከቻ ያስገባሉ (የቀጥታ መስመር ማመልከቻ የተጫኑትን የማረጋገጫ መስፈርቶች ሁሉ ማካተት ይገባዋል)
3.DSLBD ክለሳ እና ቁርጠኝነት።
ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን ይደውሉ ።
አቅም ግንባታ
የDC የጥቃቅን እና አካባቢያዊ ንግድ ስራ ልማት መምሪያ (DC Department of Small and Local Business Development (DSLBD)) በአውራጃው ውስጥ ለጥቃቅን የንግድ ስራ የሚኬድበት ሃብት ነው። ለንግድ ስራ ባለቤቶች በሁሉም የንግድ ስራ የህይወት ኡደት ውስጥ ቀጥተኛ እገዛ እና የታለሙ ፕሮግራሞችን እንሰጣለን። የእኛ ፕሮግራም እገዛዎች የንግድ ስራዎን ለማሳደግ እርስዎን በቁሳቁስ እና መሳሪያዎች ያግዝዎታል እና የበለጠ ተወዳዳሪ ይሆናሉ።
ስለ DSLBDs ፕሮግራሞች የበለጠ ለማወቅ፣ እባክዎን የእኛን የፕሮግራሞች ገፅ እዚህ ይመልከቱ። rograms page here
To become a client of DSLBD and get started with a one on one tutorial, visit our Small Business University and register.
ስለ እኛ
ተልዕኮ
የጥቃቅን እና አካባቢያዊ የንግድ ስራ መምሪያ (DSLBD) የልማት፣ የኢኮኖሚ እድገት፣ እና በአውራጃ ላይ መሰረት ያደረጉ የንግድ ስራዎችን በማደስ፣ እንዲሁም የኢኮኖሚ እድገትን በአውራጃው የንግድ ስራ ዘርፍ ውስጥ ያበረታታል።
ራዕይ
DSLBD በሚከተሉት መልኩ የንግድ ስራ ሁኔታዎችን ይተልማል፦ የDC ንግድ ስራዎች አግባብ ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ የአካባቢያዊ፣ ፌደራል እና ዓለም አቀፍ የንግድ ስራ እድሎችን፤ በፍጥነት፣ በሚስጥር እና በቅልጥፍና መንግስትን በሚዳስሱ የንግድ ስራዎች ይሳተፋል፤ እንዲሁም፣ ማንኛውም አንተርፐርነር ከፍተኛ ሃሳብ እና ዕቅዱን በንግድ ስራ እውን ለማድረግ ካፒታል አለው።